ውድ ደንበኞች፣
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንዳንድ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች አጋጥሞት በነበረው አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት ትናንት መጋቢት 6 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ መቀሌ፣ባህር ዳር፣ ላልይበላ፣ ጎንደር፣ ሁመራ፣ አክሱምና ሽሬ የሚያደርጋቸው በረራዎች መስተጓጎላቸው ይታወሳል።
ሆኖም ዛሬ መጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም ተከስቶ የነበረው የአየር ጠባይ ለውጥ በመስተካከሉ አየር መንገዱ ተሰርዘው የነበሩትን በረራዎች የቀጠለና፣ ተጨማሪ አውሮፕላኖችን በመመደብ በአገልግሎት መስተጓጎል የተጉላሉ መንገደኞችን ማጓጓዙን በአክብሮት ይገልጻል።
ወደ ደሴ የሚደረገው በረራ በአካባቢው የተከሰተው የአየር ጠባይ ለውጥ እንደተስተካከለ የበረራውን መጀመር በጥሪ ማእከላችን በኩል ለክቡራን ደንበኞቻችን የምናሳውቅ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።
ተፈጥሮ ለነበረው መጉላላት አየር መንገዱ በድጋሚ ልባዊ ይቅርታ ይጠይቃል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ