ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሰጠ መግለጫ   መጋቢት 6 ቀን 2012 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ

ውድ ደንበኞች፣

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንዳንድ የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች ባጋጠመው አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ምክንያት ዛሬ መጋቢት 6 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ መቀሌና ላልይበላ የሚያደርጋቸው በረራዎች ተሰርዘዋል። በተመሳሳይ ወደ ጎንደር፣ አክሱምና ሽሬ ይደረጉ የነበሩ በረራዎችም ዛሬ ጠዋት የተስተጓጎሉ ሲሆን፣ የአየር ሁኔታው መሻሻሉን የሚገልጽ መረጃ ከብሄራዊ ሚቲዎሮሎጂ አገልግሎት እንደደረሰን በረራውን የምንቀጥል መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።

ይህ የአየር ሁኔታ በቀጣዮቹ 2 ቀናት ሊቀጥል እንደሚችል ከሚቲዮሮሎጂ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ የሚጠቁም ሲሆን፣ በረራዎቹ ለመቀጠላቸው ከሚቲዎሮሎጂ መስሪያ ቤቱ መረጃ እንደደረሰን በጥሪ ማእከላችን በኩል ለክቡራን ደንበኞቻችን የምናሳውቅ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።

ለተፈጠረው መጉላላት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ልባዊ ይቅርታ ይጠይቃል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ