ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የተሰጠ መግለጫ

መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም፣አዲስ አበባ

ውድ ደንበኞች፣

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመቀሌ ፣ በላልይበላ ፣ በሽሬ ፣ በጎንደር ፣ በባህር ዳር እና በሑመራ ከተሞች ባጋጠመው አስቸጋሪ የአየር ጠባይ ለውጥ ምክንያት ከላይ በተጠቀሱት መስመሮች የበረራ መዘግየት አጋጥሟል ፡፡ በተመሳሳይ ወደ ደቡብ ሱዳን፣ ጁባ ሊደረግ የነበረው በረራ ወደ ኢንቴቤ እንዲቀየር ተደርጓል።

ለተፈጠረው መጉላላት ልባዊ ይቅርታ እየጠየቅን ወቅታዊ መረጃዎችን የምናደርሳችሁ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ