እንኳን ለ2011 ዓ.ም የገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ለክቡራትና ክቡራን ደንበኞቻችን

የኢትዮዽያ አየር መንገድ እንኳን ለ2011 ዓ.ም የገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የጤናና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቱን ይገልጻል። በዚሁ አጋጣሚ በሀገሪቱ በሚገኙ የቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች በተለይም በላልይበላ ውቅር አብያተ ክርስትያናት  በመገኘት በዓሉን በልዩ ልዩ ደማቅ ክርስትያናዊ  ስነ-ስርአቶቸ ለማክበር ወደ ሀገራችን ለሚገቡ ትውልደ ኢትዮዽያውያንና ዓለም አቀፍ ቱሪስቶች ልዩ የሆነና አቅምን ያገናዘበ የጉዞ ጥቅል አገልግሎት/package/ ያዘጋጀ መሆኑን ሲገልጽ ላቅ ያለ ደስታ ይሰማዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለዘንድሮ የላልይበላ በዓለ ንግስ ክብረ በዓልን ለማክበር ወደ ቦታው የሚጓዙ ከ1500 በላይ የሚሆኑ መንገደኞችን ከወትሮው በተለየ ሁኔታ በምቾት ለማጓጓዝ ዘወትር ካለው የበረራ ድግግሞሽ በተጨማሪ 9 አዳዲስ የበረራ መርሃግብሮችን የጨመረ መሆኑን አየር መንገዱ በታላቅ አክብሮት ይገልጻል።

መላው የክርስትና እምነት ተከታዮች መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ በድጋሚ እንመኛለን!!

የኢትዮዽያ አየር መንገድን ስለመረጡ ከልብ እናመሰግናለን!! 

gena